Posts
Showing posts from January, 2025
ብልፅግና አልቆ መገንባትን አስቀድሞ የሚያስብ ፓርቲ ነው
- Get link
- X
- Other Apps
"ብልፅግና አልቆ መገንባትን አስቀድሞ የሚያስብ ፓርቲ ነው"- የብልጽግና ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብልፅግና ፓርቲ ሊያፈርስ የሚፈልገውን ብቻ ማፍረስ ሳይሆን አልቆ መገንባትንም አስቀድሞ የሚያስብ ፓርቲ ነው ሲሉ የብልጽግና ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት "ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል። የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ብልፅግና ሊያፈርስ የሚፈልገው በርካታ ኋላቀር አሰራሮች እና ልምምዶች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ ቢያውቅም አልቆ መገንባትን አስቀድሞ የሚያስብ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም ነው "ፒያሳን ማፍረስ ሳይሆን አልቆ መገንባት የብልፅግና መለያው የሆነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የፓርቲ ፖለቲካ ታሪክ 60 ዓመታትን ያልተሻገረ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በእነዚህ ዓመታት የነበረን የፓርቲ ፖለቲካ ልምምድ የምንፈልገውን ለውጥ ማመላከት ላይ ውስንነት የነበረበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ "ኢትዮጵያ ውስጥ የፓርቲ ፖለቲካ ስንጀመር ብልፅግናን እስከፈጠርንበት ድረስ ያሉ ድካሞች ውድቀቶች ልንሻገራቸው ያልቻልናቸው አንድ ፓርቲ ለውጥ ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን ለውጥ መሪ መሆኑን አለመገንዘባችን ነው" ብለዋል፡፡ ለውጥ መፍጠር ብቻውን ለውጥ ለመመራት የሚያስችል ብቃት እስካልፈጠረ ድረስ የተሟላ የፓርቲ ህልውና አይኖረውም ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ለውጥ መፍጠር ማለት ስላለው ችግር ድካም ውድቀት አብዝቶ መናገር ሳይሆን መፍትሄም ማፍለቅ ይጠይቃል ነው ያሉት፡፡ "ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት ሃምሳ እና ስልሳ...