የሶማሌ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ አካሄዱ፡፡
የሶማሌ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የተመራ ልዑክ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት በመገኘት በስራ እድል ፈጠራና በሌሎች አሰራሮች ዙሪያ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ አካሂደዋል፡፡ የሶማሌ ክልል አመራሮችና ሰራተኞች እኛን መርጠው ስለመጡ እናመሰግናለን ያሉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ መለሰ ገ/ሚካኤል በጽ/ቤታችን አጠቃላይ አሰራርና አደረጃጀት እንዲሁም በቢሮ ማዘመን እንዲሁም በሌሎች ውጤታማ አሰራሮች ዙሪያ ልምዳችንን አካፍለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የሶማሌ ክልል ስራና ክህሎት ምክትል ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ መርዋ አብዲ በበኩላቸው በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጠቃሚ ልምድና ተሞክሮ ማግኘታቸውን ገልፀው የተመለከትነውን አሰራር ወደ ክልላችን ወስደን ተግባራዊ እናደርጋለን ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
ወ/ሮ መርዋ ጨምረውም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት የአዲስ ከተማ ኮሙኒኬሽን ገፆችን
ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት የአዲስ ከተማ ኮሙኒኬሽን ገፆችን
አዲስ አበባ የተሞክሮ ማእከል 👍👍👍
ReplyDelete