በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተግባራትን አልቆ መፈፀም አንዱ የፓርቲያችን የትኩረት አቅጣጫ ነው !
"በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማስተባበሪያ ዘርፍ የከተማ እና የክ /ከተማ ኃላፊዎች ያለፉትን ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም በመገምገም የዘርፉን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የጋራ አድርገዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዱልረሂም በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት ለሚደረገው ርብርብ የቴክኖሎጂን አቅም በአግባቡ መጠቀም ወሳኝ በመሆኑ ተግባራዊ የሚደረጉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ስራዎች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲያዝ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ጊዜንና ወጪን በማያባክን መልኩ መረጃዎችን ለመለዋወጥ ኦንላይን ኮንፈረንስ ሲስተም በሁሉም ክ /ከተሞች በቅርቡ ወደ ተግባር እንደሚገባ ያመላከቱት አቶ መሀመድ በሁሉም የፓርቲ ወረዳዎች ቨርፑዋል ኮኔክቲቪቲን ለማጠናከር ርብርብ እንደሚደረግም አስገንዝበዋል።
የአባላትንና የአመራሩን መረጃ በየጊዜው ማጥራትና ማዘመን፣ አዳዲስ አባላትን ወደ ዳታ ቤዝ ማስገባት ፣ የተንጠባጠቡ ስራዎችን ፈጥኖ ማስተካከል በልዩ ርብርብ ማከናወን እንደሚገባ ያስረዱት አቶ መሀመድ ከህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ዘርፍ ጋርም የጋራ ስራዎችን ለማጠናከር ቅንጅታዊ ጥረት እንደሚደረግ አመላክተዋል።
የየካ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ ፅ / ቤት የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተራማጅ ተረፈ በውይይቱ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የካን የከፍታ ማሳያ ማድረግ የሚያስችሉ ለሀገራችንም ለከተማችም ማንሰራራት ጉልህ ፋይዳ ያላቸው የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማስተባበሪያ ዘርፍ የመረጃ አያያዝ እንዲዘምንና ስራዎች በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ በማድረግ አሻራውን ለማሳረፍ የጀመራቸው ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ገልፀዋል።
የመልሶ ማደራጀት ስራዎች እንዲሳለጡ ዘርፉ የሚጠበቅበትን መወጣቱ በቀረበው ሪፖርት የተመላከተ ሲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጎልበት ፣ የተቋማትን ፣ የአመራሩን እና የአባላትን መረጃዎች በማጥራት ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የዶክሜንቴሽን ስራ በሁሉም ክ/ከተሞች ተግባራዊ በማድረግ ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ስራ በማስገባት ፣ መረጃ ማጥራትን በቁርጠኝነት በማከናወን አበረታች ተግባራት መሰራታቸውም ተጠቅሷል።
በውይይቱ ላይ ከቀረበው የዘርፉ የከተማ ሪፖርት በተጨማሪ በክ/ከተማ ደረጃ እየተከናወኑ የሚገኙ ለተሞክሮም ጭምር ሊሆኑ የሚችሉ በቴክኖሎጂ የተደገፉ ስራዎችም ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በቅርቡ ሰፍተው እንደሚተገበሩ ተገልጿል።
ጥንካሬዎችን ለማጎልበት ፣ ክፍተቶችን ደግሞ ለመሙላት ከባለድርሻ አካላት ጋር የተናበበ ርብርባቸውን እንደሚያጠናክሩ የውይይቱ ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት "





Comments
Post a Comment