የብልጽግና ፓርቲ እህት ፓርቲዎች ምስክርነት


የብልጽግና ፓርቲ እህት ፓርቲዎች ምስክርነት፦

"ኢትዮጵያ ምንጊዜም የምስራቅ አፍሪካ ምሰሶ ነች"

የጅቡቲው ፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግረስ ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ኢልያስ ሙሳ ዳዋሌ

"የኢትዮጵያዊያን የአርበኝነት መንፈስ ለፀረ ቅኝ ግዛትና አፓርታይድ ስርዓት ትግል እንዲቀጣጠል አድርጓል"

የዚምባቡዌው ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ዋና ጸሃፊ ሲምበርሼ ሙቤንጌግዊ

"የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃሳቦች የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን ብልፅግና ለማረጋገጥ ይበጃሉ"

የተርኪዬ ኤኬ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዛፈር ሲራካያ

"ጉባዔው ለኢትዮጵያ ቀጣይ እድገት አሻጋሪ እንደሚሆንና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ቦታ እንደሚያስቀጥል ባለሙሉ ተስፋ ነኝ"

የዩናይትድ ሩስያ ፓርቲ ሱፕሪም ካውንስል ቢሮ አባልና የሩስያ ፌዴሬሽን ሴናተር አንድሬ ክሊሞቭ

"በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳል የአመራርነት ጥበብ ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች ትገኛለች"

የታንዛኒያው ቻማ ቻማ ፑንዱዚ ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ኢማኑኤል ቺምቢ

"ከሁለቱ አገራት ጠንካራ ግንኙነት ባለፈ በፓርቲ ለፓርቲ መካከል የትብብር ግንኙነቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል"

የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ዌላርስ ጋሳማጌራን

"ብልጽግና ፓርቲ ቃል የገባቸውን ተግባራት የፈጸመበት መንገድ እጅግ የሚደነቅ እና ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው"

የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ዋና ጸሀፊ ፒተር ላም"የናይጀሪያና የኢትዮጵያ ግንኙነት በመከባበርና በጋራ እሴት ላይ የጸና ነው

" የናይጄሪያው ኤፒሲ ፓርቲ ምክትል ሊቀ-መንበር አልሀጅ አሊቡካር ዳሎሪ

"በአፍሪካ የአንድነት መሰረት እንዲጸና ልማትና ብልጽግና እንዲረጋገጥ በማድረግ ኢትዮጵያ የላቀ ሚናዋን እየተወጣች ነው"

የደቡብ አፍሪካው ናሽናል ኮንግረንስ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል ኑዶሎ ኪቤት








Comments

Popular posts from this blog

የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ

በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተግባራትን አልቆ መፈፀም አንዱ የፓርቲያችን የትኩረት አቅጣጫ ነው !